image
image
image
image

ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ ሁሉም ዜጋ የየበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

ጥር 21/5/2018, 2017
ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ ሁሉም ዜጋ የየበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ የልደታ ክ/ከተማ የስነ-መግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው እንደተናገሩት ሌብነት ልማትና እድገታችንን የሚጎትት በመሆኑ መንግስት ሙስናን ለማጥፋት በትኩረት እየሰራ ነው ብለው እንደ ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደርም ባለፍት 6 ወራት ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን ለማጥፋት በቅንጅት መሰራቱን ገልፀዋል። ወ/ሮ እማዋይ አክለውም ሙስናን መዋጋት የአንድ አካል ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በጋራ ልንመክተው ይገባል በማለት ተናግረዋል። ሪፖርቱን ያቀረቡት የጽ/ቤቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ አያሌው ብሩ እንደተናገሩት ሌብነትን በመዋጋት ረገድ ሁላችንም ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል ብለው ሌብነት ልማታችንን ሌብነት ፍትሀዊ ተጠቃሚነታችንን እንዲጎዳ በፍፁም እድል መስጠት አይገባም ሲሉ ተናግረዋል። በ6 ወር ከእጅ መንሻ የፀዳ አገልግሎት እንዲሰፍን በትኩረት መሰራቱንና አገልግሎትን በገንዘብ የሚሸጡ አካላትን በማጋለጥ ረገድ ውጤታማ ተግባር መከናወኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ። በቀጣይ ሙስናን መከላከል የተናጠል ስራ ሳይሆን በጋራ የምንሰራው በመሆኑ ተግባሩን በመመከት ረገድ በአንድነት መቆም አለብንም ተብሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች