image
image
image
image
image

ወጣቱ ፍትሀዊ ተጠቃሚነቱን የሚጎዳውን ሙስናን አምርሮ መታገል ይኖርበታል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ

ህዳር 18/3/2018, 2017
ወጣቱ ፍትሀዊ ተጠቃሚነቱን የሚጎዳውን ሙስናን አምርሮ መታገል ይኖርበታል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ በክ/ከተማው" ትውልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን አስልመልክቶ ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል። የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት ወጣቱ ለራሱ ብሎም ለሀገሩ ማበርከት ያለበት የላቀ አስተዋፆ ሙስናን አምርሮ መታገል ነው ብለው ሙስና የወጣቱን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የሚጎዳ የሀገርን ልማትና ዕድገት ወደ ኃላ የሚጎትት በመሆኑ ወጣቱ ሙስናን ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ ሊታገለው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ወጣቱ ሙስናን አምርሮ በመታገል እና የመልካም ስነ-ምግባር አርዕያ በመሆን ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል በማለት ገልፀዋል አቶ አሰፋ። በመልካም ስነ-ምግባር የታነፀ ወጣት ሀገርን ስለሚገነባ መንግስት ስነ-ምግባራዊ ወጣት ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት አቶ አሰፋ ሙስናን የሚፀየፍና አምርሮ የሚታገል ትውልድ መፍጠር ለመንግስት ብቻ የምንተወው ተግባር ሳይሆን የሁላችንም ኃላፊነት መሆን አለበት በማለት ተናግረዋል። በልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጄ ተሬቦ እንደተናገሩት ሙስና በመታገል ረገድ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሊሆኑ ይገባል ብለው ወጣቶች ሙስናን አምርረው ካልታገሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ሊጎዳ የሚችል ተግባር ነው በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከተታትያ ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ እማዋይ አበባው እንደተናገሩት ወጣቶች በስነ-ምግባር ታንፀው ሙስናን ግንባር ቀደም ሆነው ሊታገሉት ይገባል በማለት ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሙስና የበለጠ ጉዳት የሚያደርሰው በእኛ በወጣቶች ላይ በመሆኑ አምርረን እንታገለዋለን በማለት ተናግረዋል። በክ/ከተማው በዓለም ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች