image
image
image
image
image

በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባትና ሙስናን ለመከለል የሴቶች ሚና የላቀ ነው

ህዳር 12/3/2018, 2017
በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባትና ሙስናን ለመከለል የሴቶች ሚና የላቀ ነው ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዓለም አቀፋዊ ቀን አስመልክቶ "ትውልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል ከሴት ደረጃጀቶች ጋር ውይይት አደረገ። የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ሁሉም በትዉልድ ግንባታ ያለዉን ሚና በብቃት እንዲወጣና ተቋማትም ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጣቸዉን የአሰራር ክፍተት በጥናት እየለዩ በመዝጋት ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣት ስርዓት መዘርጋት ይገባል ብለዋል፡፡ የሥነ-ምግባርና የሞራል እሴቶች ግንባታ ማጠናከር፤ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግር ከሥር መሰረቱ እንዳይፈጠር ለማድረግ ትውልዱ በስነ ምግባር እንዲታነፅ ሁሉም ሀላፊነት አለበት ብለዋል። በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያላቸው አካላት በሙሉ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ያሉት አቶ አሰፋ አያይዘው የፀረ - ሙስና ትግል ሕዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሠራር መለየት፤ ማጋለጥና ማረም እንደሚገባ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጄ ተሬቦ ሙስናና ብልሹ አሰራር ልማትን በማዳከም የሀገር ኢኮኖሚ እንዲገታ የሞራልና የሥነምግባር ቀውስ የሚያስከትል ለእድገት ፀር በመሆኑ በጋራ ልንታገለው ይገባል ብለዋል። ሙስናን ለመከላከል በጋራ በመታገል ከተማዋ የተያያዘችውን የእድገት ጎዳና እና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲፋጠንና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የውይይቱን ተሳታፊዎችም ሰነድ የቀረበበት አግባብ የተሻለ መሆኑንን በመግለፅ በተለይ የሥነ ምግባር ባህርይ መለኪያዎች በመግለፅ ሃሰተኛ እና የተጭበረበረ ሰነድ አለመጠቀም፣ አለመስረቅ የመሳሳሉት በህግ ማእቀፍ ውስጥ ተካተው መገኘቱ በሰነዱ የቀረበበት አግባብ አስተማሪ መሆኑን በማንሳት በተለይ ሙስና ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ሥርዓቶችን፣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ አሰራሮችን፣ መርሆዎችን የመጣስ የሙስና ወንጀል መሆኑን በደንብ በመገንዘብ ተሳታፊውም ሙስናን በመከላከልና ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ መገንባት ላይ የራሱን ሚና መወጣት እንዳለበት አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች