image
image
image
image
image

የሰላም እሴትን መገንባት ለሙስና መከላከል የላቀ ሚና አለው ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ

ህዳር 17/3/2018, 2017
የሰላም እሴትን መገንባት ለሙስና መከላከል የላቀ ሚና አለው ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ አስተዳደሩ በዓለም ለ22 ጊዜ በሀገራችን ለ21 ጊዜ "ትውልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ ከሀይማኖት አባቶች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት የሰላም እሴቶችን መገንባት ሙስናን ለመከላከል የላቀ ሚና አላቸው ብለው በዚህም የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አደ ስንቄዎች እና አባገዳዎች የሰላም የእሴቶች ግንባታ ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የሰላም እሴቶችን በትውልዱ ላይ በማስረፅና በአግባቡ በመጠቀም ሙስናን የሚፀየፍ እና አምርሮ የሚታገል ትውልድ መገንባት ይገባል ያሉት አቶ አሰፋ ለዚህም ማህበረሰቡ የመሪነት ሚናውን መወጣት አለበት ሲሉ ገልፀዋል። ፍትሀዊነት ፣እኩልነትንና ግልፀኝነትን በማስፈን እንዲሁም መቻቻልንና መደጋገፍን በማዳበር ረገድ የሀይማኖት አባትች፣ ሀደ ስንቂዎች፣ አባ ገዳና የሀገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ያሉት አቶ አሰፋ ስነ-ምግባራዊ ትውልድን በማፍራት ረገድ ሁሉም የየድርሻውን ሊወጣ ይገባል በማለት ተናግረዋል። አቶ አሰፋ አክለውም የፀጥታ መዋቅሩ የሰላም እሴቶችን ተጠቅሞ ስነ-ምግባራዊ ትውልድን እውን ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል። ‎የልደታ ክፍለ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቶሎሳ መርጋ የፀጥታ አካሉ ከሰላም ሰራዊትና ከማህበረሰቡ ጋራ በቅንጅት በመስራት ሥነ-ምግባራዊና ህጋዊ መሰረት ባለው መመሪያና ደንብ ላይ ተመርኩዞ ማገልገል እንዲቻል ሁሉም ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልፀዋል ። ‎ የሙስና ወንጀል ተጋላጭነትን ለመቅረፍ በአሰራሮች ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ መኖሩ ችግሩን ለመፍታት ጠንካራና ወጥነት ያለው ትግል ለማድረግ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው በማለት አቶ ቶሎሳ ገልፀዋል። ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ለማጥፋት በቁርጠኝነት መታገል ይገባል ያሉት አቶ ቶሎሳ አያይዘው የተቀናጀ የፀረ-ሙስና ትግል በማድረግ ተቋማት ከሙስና የፀዳ ማድረግና ለዚህ ተግባር በትጋት በመስራት ውጤት ማምጣት ይገባል ብለዋል። ‎የመድረኩ ተሳታፊዎችም የነበረው ውይይት ተሻለ መሆኑን በመግለፅ ሙስና የእድገትና የልማት ፀር መሆኑን በመረዳት ሁሉም ትውልድን በስነ ምግባር በማነፅና ሙስናን በመታገል ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አንስተዋል። ‎

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች