image
image
image
image
image

ሙስናን በመከላከል ዙሪያ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ሚና ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል

ህዳር 2/3/2018, 2017
አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። የልደታ ክፍለ ከተማ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ጽ/ቤት ሙስናን በመከላከል ዙሪያ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ሚና ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ተስፋዬ ሙስናና ብልሹ አሰራር የሚፀየፍና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ውስጥ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ድረሻቸውን በመወጣት የሀገራችን ልማት እንዲፋጠንና ከሚገኘውም ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ለሀገርቱ ራዕይ እውን በመሆን የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል። ሙስናን በመከላከልና የሚጠየፍ ትውልድ ማፍራት የሁሉም ሚና ነው ያሉት አቶ አበራ ተስፋዬ አያይዘው ትውልዱ በስነ ምግባር የታነፀና ሙስናን የሚታገል እንዲሆን ሁላችንም ሀላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል በማለት ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች በፀረ-ሙስና ትግሉ ያላቸው ሚና በአግባቡ በመወጣት የነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ በስነ ምግባር የታነፀና እንዲሆን ተደርጎ እንዲቀረፅ ሁሉም ሀላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች