image
image
image
image
image

ትዉልድን በስነ ምግባር በማነፅና በተቋማት የተሻለ የአሰራር ስርአት እንዲኖር አመራሩ አርአያ መሆን ይገባዋል።"

ህዳር 9/3/2018, 2017
"ትዉልድን በስነ ምግባር በማነፅና በተቋማት የተሻለ የአሰራር ስርአት እንዲኖር አመራሩ አርአያ መሆን ይገባዋል።" ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ትውልድን በሥነ ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን 22ተኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ውይይት አካሂጿል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በዉይይቱ ላይ እንደተገለፁት የበአሉ ዓላማ በከተማችን የተጀመረዉ የትዉልድ ስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራ በንቅናቄ ተመርቶ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረዉ ማድረግ መሆኑን ገልፀዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው ትዉልድን በስነ ምግባር በማነፅና በተቋማት የተሻለ የአሰራር ስርአት እንዲኖር አመራሩ አርአያ መሆን ይገባዋል ብለዋል። የክፍለ ከተማዉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለው በበኩላቸው በአሉ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ መከበሩ፤ የፀረ ሙስና ትግልን በታማኝነትና በሀላፊነት ስሜት አመራሩ እንዲወጣ የሚያስችል እንደሆነ አንስተዋል። የፀረ ሙስና ቀን ሲከበር ትዉልድ ላይ የምንሰራዉ በመሆኑ የበአሉን አላማና ግቦች በሚያሳካ መልኩ ማከበር እንደሚገባ አቶ ፍታለው ጠቁመዋል። የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አራርሳ ድሪባ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት ትዉልድን በስነ ምግባር፤ ተቋምን የተሻለ አሰራር ስርአት እንዲኖር በመዘርጋት የትዉልድ ግንባታን በሚያጎላ መልኩ መከበር እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል። በአሉ ህብረተሰቡ ለፀረ ሙስና ትግሉ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ በሚያስችል መልኩ መከበር እንዳለበትም አቶ አራርሳ ጨምረዉ ተናግረዋል። የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የክ/ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የፓለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ሲሆኑ በዓሉን በተለያዩ ሁነቶች በማክበር የህብረተሰብ ክፍሎች የተሻለ የፀረ ሙስና ትግልን በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመስርተዉ እንዲያግዙ ለማስቻል እንደሆነ አብራርተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች