image
image
image
image
image

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በስነ- ምግባር የታነፀ ትውልድን ለመገንባትና ሙስናን ለመከላከል ሚናቸው የላቀ ነው

ህዳር 13/3/2018, 2017
"የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በስነ- ምግባር የታነፀ ትውልድን ለመገንባትና ሙስናን ለመከላከል ሚናቸው የላቀ ነው" አቶ አሰፋ ቶላ ህዳር 13/2018 የአ/አ/ከ/ስ/ፀ/ሙ/ኮ በልደታ ክ/ከተማ "ትውልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪቃል ለ21 ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው። በዛሬው እለትም በልደታ ክፍለ ከተማ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ከክፍለ ከተማው 10ሩም ወረዳ ለተወጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሙስናን አስከፊነት የሚገልጹ የኪነ-ጥበብ ስራዎች አቅርበዋል:: በኪነ-ጥበብ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሀላፊና ፖለቲካ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አሰፋ ቶላ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድን ለመገንባትና ሙስናን ለመከላከል ሚናቸው የላቀ ነው ያሉ ሲሆን ሙስና ልማትን በማዳከም የሀገር ኢኮኖሚ የሚጎዳ ፤ የሞራልና የሥነ-ምግባር ቀውስ የሚያስከትል በመሆኑ በጋራ ልንታገለው ይገባል ብለዋል። አቶ አሰፋ አክለውም ሙስናን በጋራ በመታገል የከተማዋ እድገትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲፋጠን መስራት ይገባል ብለው የከተማዋ እድገት ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በኪነጥበብ ፕሮግራሙም በክፍለ ከተማው ባህልና ኪነጥበብ የባህል ቡድን እና በተጋባዥ አርቲስቶች የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች ቀርበዋል "ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!” ለጥቆማ በነፃ የስልክ መስመር8887 https://www.facebook.com/share/1AxqPkYgNQ/ ቴሌግራም:- https://t.me/aaethics2015 ቲክቶክ:–https://www.tiktok.com/@addis.ababa.ethic?_t=ZM-8tqgdUzDifn&_r=1 ዩቲዩብ:– https://youtube.com/@addisethics?si=KYuB2L8_rwYnrtQK ኢሜል ፡- aaanticoruption@gmail.com

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች