1. ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ፓሊሲ እና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ ከተማ አቀፍ ፖሊሲና ስትራቴጂ ያዘጋጃል፣ ለምክር ቤት ያቀርባል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
2. በከተማው አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶች እና በህዝባዊ ድርጅቶች የሚሾሙ ወይም የሚመደቡ ወይም የሚቀጠሩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የሥነ-ምግባር እና የሙስና መከላከል ሥልጠና እንዲወስዱ ያደርጋል፣
3. በአስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ፣ በልማት ድርጅቶች እና በህዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጡ እና ሊጋለጡ የሚችሉ የአሠራር ሥርዓቶችን በማጥናት ወይም እንዲጠኑ በማድረግ የተሰጡ የመፍትሔ ወይም የማሻሻያ ሃሣቦችን ያቀርባል፣ ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣ በማይፈፅሙት ላይ ተገቢ የሆኑ እርምጃ እንዲወሰድ በሕግ የመመርመርና የመክሰስ ሥልጣን ላለው አካል ያቀርባል፣
4. የከተማው ነዋሪ ሕዝብ ተመራጮች፣ የአስተዳደሩ ተጠቃሚዎች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የአስተዳደሩ የልማት ድርጅቶች እና የሕዝባዊ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሀብታቸወን እንዲያሳውቁ፣ እንዲያስመዘግቡ፣ ትክክለኛነቱ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤ መረጃውን በአግባቡ አደራጅቶ ይይዛል፤ ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል