image
image
image
image
image

ወጣቶች በፀረ ሙስና ትግል ውስጥ ያላቸውን ሚና

ህዳር 7/3/2018, 2017
"በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" በልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶች በፀረ ሙስና ትግል ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲያጠናክሩ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ የሙስናን አውዳሚነት በመረዳት ብልሹ አሰራርን የሚጸየፍና በንቃት የሚታገል ትውልድን ለመፍጠር በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት፣ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ለልደታ ክ/ከተማ ወጣት ማህበር አመራሮችና አባላት ስልጠና ሰጥቷል። "ሙስናን ከመከላከል አንጻር የወጣቶች ሚና" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ፣ ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆኑ የዛሬ የለውጥ አጋሮች እንደመሆናቸው መጠን በፀረ ሙስና ትግሉ ውስጥ ያላቸውን የማይተካ ሚና እንዲገነዘቡት ማድረግ ዋነኛ ዓላማው እንደነበር ተገልጿል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ተስፋዬ ሙስና የሀገርን ልማት የሚያቀጭጭ፣ ማህበራዊ ፍትህን የሚያዛባና መልካም አስተዳደርን የሚጎዳ ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። አቶ አበራ አክለውም ወጣቱ ትውልድ በጉልበቱ፣ በእውቀቱና በንጹህ ህሊናው ይህንን አውዳሚ ተግባር ሊታገለውና የለውጡ አራማጅ ሊሆን ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። የክፍለ ከተማው ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው እንደተናገሩት ወጣቶች ሙስናን ሲመለከቱ ጥቆማ መስጠት የሚችሉባቸውን መንገዶች፣ የመረጃ ሰጪዎች ደህንነት እንዴት እንደሚጠበቅና የህግ ማዕቀፎችን በማብራራት ለተሳታፊዎች በቂ ግንዛቤ አስጨብጠዋል። ስልጠናው ወጣቶች በፀረ ሙስና ትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና በግልጽ እንዲረዱና ለቀጣይ ተግባራት እንዲነሳሱ ትልቅ መነቃቃት የፈጠረ መሆኑን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል። ይህ አይነቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። በመጨረሻም የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር፣ ከወጣቶች ጋር በመተባበር ሙስናን የመከላከል ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች