image
image
image
image
image

የፀረ ሙስና ትግሉን ከግብ ለማድረስ በሙስና ወንጀል ህጎች ላይ በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ መያዝ እንደሚገባ ተገለፀ።

ታህሳስ 17/4/2018, 2017
የፀረ ሙስና ትግሉን ከግብ ለማድረስ በሙስና ወንጀል ህጎች ላይ በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ መያዝ እንደሚገባ ተገለፀ። የልደታ ክፍለ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል በክፍለ ከተማው ለሚገኙ የመንግሥት ሰራተኞች በሙስና ወንጀል ህጎች ዙሪያ የተዘጋጀና በተቋማት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን መከላከል የሚያስችል የግንዛቤ መስጫ ስልጠና ተሰጠ። በተቋማት የሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ለመንግሥት ሰራተኞች በቅድሚያ ግንዛቤ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ የልደታ ክ/ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ባለሞያ የሆኑት አቶ አያሌው ብሩ ጠቁመዋል። አቶ አያሌው አያይዘው በዚህ ስልጠና የሙስና ወንጀል ትርጉም ምንነት እና አይነት፤ የሙስና ወንጀል ከሌላው ወንጀል አንፃር ልዩ ባህሪያት ምን እንደሆኑ እና ተቋማትና ሰራተኞቻቸው ይህን ወንጀል ለመከላከል ምን አይነት ተቋማዊ አሰራርና ባህሪ ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን ግንዛቤ ለመስጠት እንደሆነ ገልፀዋል። በልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ኬሎ ካሳ በበኩላቸው በሙስና መከላከልና መቆጣጠር ህጎች ላይ ግንዛቤ በመስጠት ብልሹ አሰራርና ሙስና ላይ ትግል ለማድረግ እና ግንዛቤ በመፍጠር በሌብነት ድርጊት ላይ የሚሳተፉትን ተጠያቂ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልፀው በሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 ተፈፃሚነት ላይ በዝርዝር አብራርተዋል። ሙስና የአንድን ሀገር መልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የሰብዓዊ መብት መከበር በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ፣ ሐቀኝነትን በማጓደል የህገ-ወጥነትን ባህሪ የሚያላብስ እና ሀገርን ሊበትን የሚችል ወንጀል መሆኑን አቶ ኬሎ አስገንዝበዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በስራ ስነ-ምግባር ላይ ራሳቸውን በማነፅ በተቋማት የሚፈፀሙ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ፀር የሆኑ የተለያዩ የሙስና ወንጀሎችን መታገል የሚያስችላቸውን አቅም እንደፈጠረላቸውም ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች