image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ የስነ-መግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።

ሀምሌ 14/11/2017, 2017
ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ ሁሉም ዜጋ የየበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ የልደታ ክ/ከተማ የስነ-መግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የስነ-መግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ሌብነት ልማትና እድገታችንን የሚጎትት ነው ብለው በዚህም መንግስት ሙስናን ለማጥፋት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የስነ-መግባርና ፀረ ሙስና ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ሌብነትን ለማጥፋት ከተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ብለው በዚህም በበጀት ዓመቱ ስኬት መመዝገቡን ገልፀዋል። ወ/ሮ እማዋይ አክለውም ሙስናን መዋጋት የአንድ አካል ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በቀጣይ በጋራ ልንመክተው ይገባል በማለት ተናግረዋል። የጽ/ቤቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ አያሌው ብሩ እንደተናገሩት ሌብነትን በመዋጋት ረገድ ሁላችንም ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል ብለው ሌብነት ልማታችንን እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነታችንን እንዲጎዳ በፍፁም እድል መስጠት አይገባም ሲሉ ተናግረዋል። አቶ አያሌው አክለውም በበጀት ዓመቱ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለማክሰም በትኩረት ሰርተናል ብለው በቀጣይ ይህ ተግባር ተጠናክሮ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የፀዳች ክፍለ ከተማ ለመፍጠር የምናደርገውን ራዕይ ልናሳካ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በበጀት አመቱ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመመከት የተሰራው ስራ ስኬታማ እንደነበረ ገልፀዋል። ባለፍት 12 ወራት ከእጅ መንሻ የፀዳ አገልግሎት እንዲሰፍን በትኩረት መሰራቱንና አገልግሎትን በገንዘብ የሚሸጡ አካላትን በማጋለጥ ረገድ ውጤታማ ተግባር መከናወኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ። በቀጣይ ሙስናን መከላከል የተናጠል ስራ ሳይሆን በጋራ የምንሰራው በመሆኑ ተግባሩን በመመከት ረገድ በአንድነት መቆም አለብንም ተብሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች