image
image
image
image
image

ሴቶችን ያማከለ የሥነ ምግባር ግንባታ ሙስናን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።

ሰኔ 4, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ሴቶችን ያማከለ የሥነ ምግባር ግንባታ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚኖረው ፋይዳ ላይ ያተኮረ ስልጠናና የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እናትዓለም እንዳለ እንደተናገሩት ሴቶች ሙስናን በመጸየፍ ረገድ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆን እንዳለባቸው ገልፀው ሴቶች በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ የሥነ ምግባር ምሰሶ በመሆናቸው ይህንን ተጠቅመው ሙስናን መከላከል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ መንግሥት ሴቶችን በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ በንቃት ለማሳተፍ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ማህበሩም የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በስልጠና መድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ምላሽ የሰጡት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው ሴቶች ሙስናን በመከላከል ረገድ ቀዳሚ መሆን አለባቸው ብለው መንግስት ሙስናን ለማጥፋት እየሰራው ላለው ስራም አጋዥ መሆን አለባቹህ ሲሉ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ ገነት ገብረመድህን የሥነ ምግባር ግንባታ ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ጀምሮ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባና ሴቶች ልጆቻቸውን በሥነ ምግባር በማነጽ ረገድ ሊጫወቱት የሚችሉትን ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል። ስልጠናውን የሰጡት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ መላኩ ጌታሁን በበኩላቸው፣ የሙስና ምንነት፣ መገለጫዎቹ፣ በሀገርና በማህበረሰብ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንዲሁም ሴቶች በሙስና መከላከል ሂደት ውስጥ ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ በተመለከተ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች በውይይቱ ላይ ስልጠና በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ ነው ብለው እኛ ሴቶች በየደረጃው ሙስናን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን ግልጽ አቅጣጫ አስቀምጦልናል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች