image
image
image
image

ጉበኝነትና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊ አሰራር እና በሕዝብ ተሳትፎ ለማምከን መግባባት ላይ ደርሰናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጥር 18/5/2018, 2017
ጉበኝነትና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊ አሰራር እና በሕዝብ ተሳትፎ ለማምከን መግባባት ላይ ደርሰናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥር 18/2018 ዓ.ም የአ/አ/ከ/ስ/ፀ/ሙ/ኮ ጉበኝነትና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊ አሰራር እና በሕዝብ ተሳትፎ ለማምከን መግባባት ላይ መደረሱን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል። “በትጋት አዲስ አበባን ወደ ላቀ ስኬት!” በሚል መሪ ሃሳብ ባለፉት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረውን የከተማችን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የመንግሥትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ በስኬት መጠናቀቁን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል። በግምገማውም ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፍ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ውጤት መምጣቱን እንደተግባቡ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡ ከሕዝቡ ቅሬታ ከሚቀርብበት የአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር በ’መሶብ’ የአገልግሎት አሰጣጥ የ94 በመቶ የህዝብ እርካታ ማግኘት መጀመራችን ለቀጣይ ስራችን ትልቅ ስንቅ መሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። በቀጣዮቹ 6 ወራትም ትኩረት የሚሹ የአመራር አፈፃፀም ልዩነቶችን በማጥበብ፣ ተቋማዊ ግንባታን ለማጠናከር፣ ጉበኝነትና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊ አሰራር እና በሕዝብ ተሳትፎ ለማምከን መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል። የከተማችንን ነዋሪዎች በተሻለ ትጋትና ታማኝነት ለማገልገል፣ የመረጃ አያያዝን ለማዘመን እንዲሁም የኑሮ ውድነትን ጫና በመቀነስ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን ለመስራት መግባባት ላይ የተደረሰበት ውጤታማ መድረክ እንደነበርም ጠቁመዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች