image
image
image
image
image

በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት ት/ቤቶች ወሳኝነት እንዳላቸው የልደታ ክ/ከተማ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታታያ ክፍል ገለፀ።

ግንቦት 14, 2017
የልደታ ክ/ከተማ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው እንደተናገሩት 11 በሚሆኑ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሚገኙ የግብረ -ገብና ስነ-ምግባር ክበባት የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል ብለው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ዋና ዓላማም በት/ቤቶች በስነ-ምግባር የታነፀ እና ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለማፍራ መሆኑን ገልፀዋል። ቡድን መሪዋ አክለውም ክበባቱን የማጠናከር እና ትውልድ የሚቀረፅባቸው እንዲሆኑ ይሰራል ብለው በጥያቄና መልስ ውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች የሰርተፍኬት ሽልማት መሰጠቱንም ጠቁመዋል። በደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትም የተሞክሮ ልውውጥ መካሄዱን ወ/ሮ እማዋይ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች