image
image
image
image

ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች እውቅና ሰጠ።

ነሀሴ 14/2018, 2018
ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች እውቅና ሰጠ። ነሀሴ 14/2018 አ/አ/ስ/ፀ/ሙ/ኮ የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2018 በጀት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የእውቅና መርሃ ግብር አካሄደ። በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበጀት ዓመቱ ከግንዛቤ ፈጠራና ማስተማር ሥራዎች ጎን ለጎን የሙስና ጥቆማዎችን በመከታተልና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን ገልፀዋል። አክለውም ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሰራሮችን በመፈተሽና ተጠያቂነትን በማስፈን ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ አሰራር እንዲዘረጋ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት በሆኑት በስነ ምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል ረገድ በበጀት ዓመቱ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በምዘና ሂደት በመለየት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ክፍሎች እውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ ገልፀዋል። አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ መከታተያ ክፍሎችም ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲመጡ በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ኮሚሽነሯ ገልጸዋል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሀብታሙ ፈይሳ የሙስና መከላከል ሥራውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ እንደሚገባ በመናገር በቀጣይ የሀብት ምዝገባን በዘመናዊ ሶፍትዌር ሲስተም በመተግበር ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት እና ከኅብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አመርቂ ለውጥ ለማስመዝገብ መታቀዱን ጠቁመዋል። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል። ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!” ???????????????????????? ለጥቆማ በነፃ የስልክ መስመር 8887 Facebook https://www.facebook.com/share/1AxqPkYgNQ/ ቴሌግራም:- https://t.me/aaethics2015 ቲክቶክ:–https://www.tiktok.com/@addis.ababa.ethic?_t=ZM-8tqgdUzDifn&_r=1 ዩቲዩብ:– https://youtube.com/@addisethics?si=KYuB2L8_rwYnrtQK ኢሜል ፡- aaanticoruption@gmail.com

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች